መንግሥት ኢንቨስትመንትን በአጠቃላይ የግል ኢንቨስትመንትን በአገራችን ለማበታትና ለማስፋፋት በ1984 ዓ.ም የመጀመሪያውን የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 15/1984 ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የሃገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ አውጥተው ኘሮጀክቶቻቸውን ተግባራዊ አድርገዋል፡፡
ይሁንና አዋጅ ቁጥር 15/1984ን በመተግበር ረገድ ያጋጠሙ ችግሮችን ለማቃለልና የዓለም ተጨባጭ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የውጭ ባለሀብቶች የሚሳተፉባቸውን የሥራ መስኮች በማስፋት እና የሚሰጡ ማበረታቻዎችን ግልጽ በማድረግ ኢንቨስትመንትን በተሻለ ሁኔታ ለማበረታታና ለማስፋፋት አዋጁ በአዋጅ ቁጥር 37/1988 (ከማስፈጸሚያ ደንቡ ቁጥር 7/1988 ጋር) በ1988 ዓ.ም እንዲተካ ተደርጓል።
በመቀጠልም በኣገሪቱ ባሉ ክልሎች የሚደረገው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግሥት በ1994 ዓ.ም ያወጣውን የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ ለማስፈጸም በሚያስችል መልኩ እንዲመራ የኢንቨስትመንት አዋጁንና የማበረታቻ ደንቡን ማሻሻል በማስፈለጉ አዋጅ ቁጥር 286/1994 እና የማስፈጸሚያው ደንብ ቁጥር 84/1995 እንደ ቅደም ተከተላቸው በ1994 ዓ.ም እና በ1995 ዓ.ም ወጥተው በሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል። የከተማ አስተዳደሩም የቀረጻቸዉን ስትራቴጂዎች እንዲያስፈጽሙ ከተቋቋሙት መስሪያ ቤቶች መካከል የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ሴክተር እንዱ ሲሆን በስሩም የኢንቨስትመንት ኤጀንሲም በ 1995 ዓ.ም ተቋቁሟል።
አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
ኮሚሽኑ የከተማዋን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በባለቤትነት የመምራትና የማስተባበር ተልዕኮውን ለመወጣት እንዲችል የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ በቀጣዮቹ ዓመታትም በዋነኝነት ሰፊ የሰው ሀይል፣ የአገር ውስጥ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት በስፋት በሚጠቀሙ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያደርጉ፣ ወጪ ምርቶችን በስፋት የሚልኩ እና የገቢ ምርቶችን በመተካት የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በማተኮር የሚሰራ ነው፡፡
የተቋሙ ስልጣን፣ ተግባርና
ኃላፊነት
የኮሚሽኑ መዋቅር እና አደረጃጀት
ወ/ሮ አይሻ መሀመድ
ዋ/ኮሚሽነር
አቶ ግርማ ቤካ
የአንድ ማዕከል ዘርፍ ም/ኮሚሽነር
አቶ ኃይሉ ሉሌ
የጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ዳኛቸው ገብሩ
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ክትትል ድጋፍ ዘርፍ ም/ኃላፊ
አቶ ተስፋዬ ኦሜጋ
የኮሚሽነር አማካሪ
አቶ መሰረት ሁንደማ
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት
ወ/ሮ ሰላማዊት ጌታቸው
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ማምረቻ ዘርፍ ክትትልና ድካፍ ዳይሬክቶሬት
አቶ ብሩክ እስተዚያ
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት አገልግሎት ዘርፍ ክትትልና ድካፍ ዳይሬክቶሬት
ወ/ሮ ወርቅነሽ ፈይሳ
የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
አቶ አየለ ደምለው
የለውጥ እና መልካም አስተዳደር ቡድን
ወ/ሮ ነጻነት መልካሙ
የህግ አገልግሎት ቡድን
ወ/ሮ መሰረት ወ/ማርያም
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ወ/ሮ ራሄል ይርዳው
የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት
አቶ ያለምሰው ሁነኛው
የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት
ወ/ሮ መቅደስ አማኑኤል
የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት
አቶ ዳምጤው በለጠ
የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት
ወ/ሮ አለም በቀለ
የግዢ ዳይሬክቶሬት
ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን
ይጎብኙን!
እርስዎን ለመርዳት እና ማንኛውንም ጥያቄ ለመመለስ እዚህ ተገኝተናል። ከእርስዎ ለመስማት በጉጉት
እንጠባበቃለን።ቡድናችን ሁሉንም ጥያቄዎችዎን ለመመለስ ደስተኛ ነው።