#አዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ዕድሎችና አማራጮች በአገልግሎት ዘርፎች

በአገልግሎት ዘርፍ

በአዲስ አበባ ከተማ ሲቋቋሙ ለባለሀብቱ ብሎም ለከተማይቱ ከፍተኛ አቅም ይሰጣሉ ተብሎ የተለዩ ዋና ዋና የማምረቻ ኢንዱስትሪ የሥራ መስኮች (የጨርቃጨርቅና የቆዳ ውጤቶች) ምግብና መጠጥ ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች' ብረት ነክ ያልሆኑ ሚኒራሎች'የብረታብረት ምርቶች ኤሌክትሮ ሜካኒካል በእንጨት ስራ ኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶችን ማምረት የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረት የጎማ ውጤቶችን ማምረት ወዘተ ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ አገሪቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከውጭ የምታስገባቸው የምርት አይነቶች ናቸው።

ኢንቨስትመንት ዕድሎች

የትምህርት ዘርፍ

የአጠቃላይ ትምህርት ዋና ዓላማ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል፤ የጐልማሶች ትምህርትና ሥልጠናን ጨምሮ ለዜጐች ጥራት ያለው ትምህርት በመደበኛና መደበኛ ባልሆነ መልኩ በመስጠት ለሥራና ለከፍተኛ ትምህርት ማዘጋጀት ነው። ይህን ዓላማ ለማሳካት የአጠቃላይ ትምህርት በአራት ዘርፎች የተደራጀ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የትምህርት ልማት ዘርፍ ነው።

የጤና አገልግሎት ዘርፍ

ምንም እንኳ ባለፉት በርካታ አስርት ዓመታት ውስጥ አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች (LMICs) ውስጥ የዜጎች የጤና ሁኔታ የተሻሻለ ቢሆንም፣ በርካታ አዳዲስ እውነታዎችም ተፈጥረዋል። የተለወጡ የጤና አጠባበቅ ፍላጎቶች፣ እያደጉ ያሉ የማህበረሰብ ጥያቄዎች እና ከፍ ያሉ የጤና ግቦች የተሻሻሉ የጤና ሁኔታዎችን እና የላቁ የማህበራዊ እሴት ለመፍጠር የጤና አጠባበቅ ስርዓቶች ማከናወን ያለባቸው ጉዳይ እንዲጨምር አድርጓል።

ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ

ዓለም አንድ መንደር ሆነች ሲባል በሌላ አገላለፅ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ተሳሰረች ማለት ነው:: የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ከሌሎች ቴክኖሎጂዎች ጋር ሲነፃፀር ገና በለጋ እድሜው በሰው ልጆች ዘንድ ተቀባይነትና እምነት አግኝቷል::

የኮንስትራክሸን ዘርፍ

መንግስት በቀጣይ አስር ዓመታት የግንባታ ዘርፍን በማዘመን ተወዳዳሪ እንዲሆን ግብ ተጥሎ እየሠራ ይገኛል።ለዚህም መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ የሚመረቱ የግንባታ ግብአቶች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ተጠንተው ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማስቻል በትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

Scroll to Top