በመዲናዋ ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ1700 በላይ ባለኃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስዷል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አይሻ መሀመድ
ህዳር/2018 ዓ .ም
በአዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ባለሐብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አይሻ መሀመድ እንደገለጹት፤ በ2018 በጀት ዓመት 2 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከ1745 በላይ ባለሐብቶች ፍቃድ ወስደዋል፡፡
ኮሚሽኑ ባለፉት አራት ወራቶች 1745 አዲስ ፍቃድ 112 ማስፋፊያ 152 ማሻሻያ 779 የእድሳት አገልግሎት መስጠቱ የገለጹት ኮሚሽነራ ኮሚሽኑ ለባለሐብቶቹ የኢንቨስትመንት አዋጁ የሚፈቅድላቸው የተለያዩ ማበረታቻዎችን እያቀረበ እንደሚገኝም ጠቁመው፤ በዚህ በጀት ዓመት የካፒታል ዕቃ 286 የግንባታ እቃ 34 ተሸከርካሪ 2 መለዋወጫ 13 የግብር እፎይታ ለ31 ባለሀብቶች መሰጠቱ ተናግሮዋል ፡፡
አያይዘውም ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ከ2 ሺህ አምስት መቶ በላይ ለሚሆነ ዜጎችም የስራ ዕድል ባለፉት አራት ወራት መፈጠሩ አስታውቀዋል።
በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማዘመን የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ፣ አዲስ አበባ ያላትን እምቅ ሀብት በማስተዋወቅ እና መዲናችን አሁን ያለችበት ቁመና የሚመጥን አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ማሳለጥ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በቅንጅት የመፍታት ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
ኢንቨስትመንቱን ለማሳደግ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሯ፤ ባለፉት ወራቶች የማምረቻው ዘርፍ አፈፃፀም ከሌሎች ዘርፎች ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰዋል።